News
Local

አዲስ የግምገማ ሪፖርት ቀጠናዊ የአየር ንብረት ፕሮግራም አሳሳቢ ጉዳዮችን ለመቅረፍ እገዛ አደረገ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ እንቅስቃሴ ትስስርን ለማጎልበት ተጨማሪ ስራዎች እንደሚያስፈልጉ አፅኖት ሰጠ።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ የዜጎች ስደት እና መፈናቀል እንዲጨምር አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአየር ለውጥ ምክንያት የሚከሰትን መፈናቀልን ለመከላከል እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሰዎች እንቅስቃሴን እውን ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ቀጠናዊ አደጋን የመከላከል አቅምን ማጎልበት  ከምንጊዘውም በላይ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪም አካባቢያዊ ኢኮኖሚዎችን ወደ አረገጓዴ ኢኮኖሚ እንዲሸጋገሩ እና ዘላቂነት ያላቸው ገቢ ማስገኛ መተዳደሪዎችን መጎልበት አለባቸው፡፡ ነገር ግን እስከአሁን ባለው ሁኔታ የተወሰኑ ሊባሉ የሚችሉ ቀጠናዊ ተግባራት ብቻ ተከናውነዋል፡፡

በፍልሰት ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና አክዚዮም ኢንተርናሽናል የወጣው የግምገማ ሪፖርት እንዴት የጋራ መርሀግበሩ (በኢጋድ ቀጠና ውስጥ በሚከሰት የአየር ንበረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ስደቶችን እልባት መስጠት እና የተቀናጀ ደህንቱ የተጠበቀ መደበኛ ስደትን ማመቻቸት) (ወይም Migration, Disasters and Climate Change, MDCC) ውስብስብ የሆነውን የአየር ንብረት፣ የተፈጥሮ አደጋ እና የሰዎች እንቅስቃሴ ጋር የተያዘዘውን ፈተና መቅረፍ እንደሚቻል አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ሪፖርቱ ከተግባራቱ የተወሰዱ ልምዶችን ከማካተቱም ባሻገር እንዴት የወደፊት ፕሮገራሞችን የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል አካቷል፡፡

ይህ 2.15 ሚሊዮን ዶላር መርሃ ግብር  ከየካቲት 2013 እስከ ነሀሴ 2015 ያለውን ጊዜ የሸፈነ ሲሆን፡፡   በአራት የመንግስታቱ ድርጅት ኤጀንሲዎች ከቀጠናዊ አጋሮች ጋር በመሆን ተተግብሯል፡፡ የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) የአደጋ መፈናቀል መድረክ (PDD) የተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎቶች ቢሮ (UNOPS) እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ጋር በመሆን የተተገበረ ሲሆን።  መርሃ ግብሩ የተካሄደው ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) እና የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል (ICPAC) ጋር በመተባበር ነው። MDCC የመጀመሪው በፍልስት ብዝሃ አጋር ትረስት ፈንድ የሚደፍ ሃሳብ ሲሆን፣ ትግበራውም ሉላዊ የሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተቀናጀ እና መደበኛ ፍልሰትን ማገዝ ነው፡፡

በፍልሰት ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና በአክዚዮም የተደረገው የግምገማ ውጤት እንደሚያመለክተው ከሆን MDCC ቀጠናዊ ለሆኑ ፈታኝ ጉዳዮች ከድንበር ተሸጋሪ የተፈጥሮ አደጋዎች መፈናቀል ቅድመ ዝግጅት እስከ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ገቢ ማስገኛ መተዳደሪዎች ድረስ ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ MDCC በተፈጥሮ አደጋዎች የመፋናቀል ስጋት ላይ ማለትም በጎርፍ እና አውሎ-ነፋስ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎችን ኢጋድ ቀጠና እንዲሁም ለአባል ሀገሮቹ አዳዲስ መረጃዎችን አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ፕሮግራሙ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ብሄራዊ እና አካባቢያዊ ፖሊሲዎችን ለመገምገም፤ እንዲሁም የተፈጥሮ አደጋዎችን መከላከል ላይ እና አረንጋዴ ኢኮኖሚ ያካተተ የሰዎችን እንቅስቃሴን ከግት ውስጥ ያስገባ ዋና የአተገባበር ሰርዓት ከቀጠናው መንግስታት ጋር በትብብር ሰርቷል፡፡

የፍልሰት ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና የአክዚዮም ሪፖርት ይፋ እንዳረገው ከባላደርሻ አካላት የተደረገው ሰፈ ያለ የጋራ ትግበራ በችግሩ ዙረያ የጋራ መግባባት ብሎም የሀገር ውስጥ ግዥ እንዲጎለበት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ለምሳሌ በኬንያ የቱርካና ካውንቲ መንግስት በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሚከሰት የሰው ልጆች እንቅስቃን፣ የአየር ንብረት ለውጥን እንዲሁም የአካባቢ መራቆትን ከግምት ውስጥ ያስጋባ የልማት እቅድ ማዘጋጀት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም ከመንግስት በጀት እንዲደገፍም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡   በተጨማሪም በኡጋንዳ በኬንያ እና በኢትዮጲያ በተፈጥሮ አደጋ ጊዜ ሊኖር ስሚችል መፈናቀል ልምምድ የተደረ ሲሆን፤ ይህ ልምምድ ብሔራዊ እና አካባቢያዊ ባለስልጣናትን እንዲሁም የሲቪክ ማህበራትን ያካተተ ሲሆን ይህም በሚወጡ የስደተኞች የመቀበል እና የማቆየት አሰራሮች ላይ ሁሉንአቀፍ መግባባት እንኖር ያገዘ ነው፡፡ እነኚህ ተግባራት በሚከናወኑበት ጊዜ የእንቅስቃሴ ገደቦች፣ የኮቪድ-19 ወረሺኝ እና የደህንነት ችግች የትግበራው አፈፃፀም ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል፡፡      

የሪፖርቱ ቁልፍ ምክረሃሳቦች የሚከተሉትን ነጥቦች አስፈላጊነት ያጎላሉ፡

  • መረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ እና መርሃግብሮች እንዲኖሩ በአየር ንብረትለውጥ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ዙሪያ ላይ ያሉ መረጃዎች ትንታኔ መጎልበት እና መሻሻል እነዳለበት
  •  ተጨማሪ የቴክኒክ እና የፖሊሲ ድጋፍ የሚደረግባቸውን ቦታዎች ለመለየት የኢጋድ አባል ሀገራትን ያሳትፉ የቀጠናዊ ልምድ ልውውጦች ያስፈልጋል
  • ድንበር ተሸጋሪ ለሆኑ ፍልሰቶችን ያማካለ ስልታዊ የሆኑ አሰራሮች ላይ ኢንቨስት ማድረግ
  • አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማበልፀግ የሚያስችሉ እድሎችን መፈለግ

ምንም እንከኳን MDCC አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን ምላሽ የሰጠ ቢሆንም፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጨማሪ ጥረቶችን በማከል 2013 ጀምሮ የተገኙ መልካም ልምዶችን በማጎልበት እና ማብዛት ያስፈልጋል፡፡     

 ዘገባውን እዚህ ያንብቡ፡- here

ስለ MDCC ስራ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ ይህን ድህረ ገጽ ይጎብኙ

 

ለተጨማሪ የሚዲያ ጥያቄዎች እና መረጃ፣ እባክዎን የሚከተሉትን ግለሰቦች ያነጋግሩ፡- Yvonne Ndege, Regional Public Information Officer, IOM Regional Office for the East and Horn of Africa ronairobimcu@iom.int

Noora Makela, Programme Officer, IOM Regional Office for the East and Horn of Africa Nkmakela@iom.int

In Ethiopia: Krizia Kaye Viray, Media and Communications Coordinator, kkviray@iom.int